አሜሪካ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 331 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አደረገች።

ለሥራ ጉብኝ አዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለኢትዮጵያ ከ331 ሚሊየን ዶላር በላይ የሰብአዊ ድጋፍ ይፋ አድርገዋል።

አንቶኒ ብሊንከን እንዳስታወቁት ድጋፉ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እና በአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አማካኝነት የሚሸፈን ነው፡፡

ድጋፉም በተለያዩ ምክንያቶች በችግር ለተጋለጡ ወገኖች ለምግብ፣ ለመድሃኒት፣ ለንጹህ የመጠጥ ውሃ የሚውል መሆኑን ገልፀዋል።

ይህም በግጭት ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ፣ በድርቅ ለተጠቁ እና ለምግብ እጥረት ለተጋለጡ ዜጎች ሕይወት አድን ድጋፍ ማድረግ ያስችላል ተብላል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *