Yekatit12hospital

ኢትዮጵያ የዳሌና ጉልበት መገጣጠሚያ ንቅለ ተከላ ሕክምና መስጠት ጀመረች

ኢትዮጵያ የዳሌና ጉልበት መገጣጠሚያ ንቅለ ተከላ ሕክምና መስጠት ጀመረች

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙሉ ዳሌና ጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ ህክምና በየካቲት 12 ሆስፒታል መሰጠት ተጀመረ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአጥንት ቀዶ ህክምና እና የመገጣጠሚያ ቅየራ ከፍተኛ ቀዶ ህክምና አገልግሎትን በይፋ መሰጠት መጀመሩን አስታውቋል። የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና የመገጣጠሚያ ቅየራ እንዲሁም የአርትሮስኮፒ  ህክምና ሠብ ስፔሻሊስት ሃኪም የሆኑት ዶ/ር ሰኢድ መሐመድ እንደተናገሩት  በአሁኑ ወቅት የሙሉ ዳሌ እና ጉልበት መገጣጠሚያዎች ቅየራ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና አገልግሎትን ሆስፒታሉ በይፋ መስጠት ተጀምሯል። በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዳን የዳሌ መገጣጠሚያ ሙሉ ለሙሉ በማስወገድ በሌላ  ሰው ሰራሽ በሆነ አካል በመተካት ይህ አይነቱ ህክምና እንደሚሰጥ ተገልጿል። ይህ አገልግሎት በኢትዮጵያ ህክምና ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሠጥ ሲሆን በዳሌና…
Read More