Visaservice

የቪዛ ጊዜያቸውን ያሳለፉ ከ36 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ተቀጡ

የቪዛ ጊዜያቸውን ያሳለፉ ከ36 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ተቀጡ

በኢትዮጵያ የተሰጣቸውን የቪዛ ጊዜ ያሳለፉ ከ36 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ተቀጥተው ወደ ሕጋዊ መስመር ተመልሰዋል አለ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፡፡ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት እንዳሉት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ እየተሰራ ነው፡፡ በዘርፉ በተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ሀገራዊ አቅም መጠናከሩን አመልክተዋል፡፡ ለአብነትም በአዲስ አበባ በተካሄዱ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ጉባዔዎች የተሳተፉ የውጭ ሀገራት ዜጎች ያለምንም እንከን መስተናገዳቸውን ጠቅሰዋል። በቪዛ አገልግሎት ወደ 188 ሀገራት የመዳረሻ (ኦን አራይቫል ቪዛ) ተጠቃሚዎች ሆነዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ÷ ይህም የ24 ሰዓት የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ አገልግሎት ያለው መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ከፓስፖርት አገልግሎት ጋር በተያያዘ የተለያዩ የማሻሻያ ርምጃዎች መወሰዳቸውን እና በዚህም በሕገ ወጥ ሰንሰለት የተሰማሩ 26…
Read More