Travelrestrictions

ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ባሉ ዲፕሎማቶች ላይ የጉዞ ገደብ ጣለች

ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ባሉ ዲፕሎማቶች ላይ የጉዞ ገደብ ጣለች

መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዲፕሎማቶች ለመንግሥት ሳያሳውቁ ከከተማ እንዳይወጡ ደብዳቤ ተላከላቸው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መቀመጫውቸን በአዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ለመንግሥት ሳያሳውቁ ከከተማ እንዳይወጡ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአገሪቱ ድንበር ውስጥ ለሚያደርጓቸው ማናቸው እንቅስቃሴዎች ቅድመ ፈቃድ እንዲጠይቁ አሳስቧል፡፡ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ተቋማት፣ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ድርጅቶችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ከአዲስ አበባ ውጭ የሚያደርጓቸውን ጉዞዎች በተመለከተ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በተቀመጠ የቅድሚያ ማሳወቂያ ፎርም ከሞሉ በኋላ መሆን እንዳለበት አመላክቷል፡፡ ይሁን እንጂ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ የተጻፈው ደብዳቤ ማስጠንቀቂያው ለሥራ ወይም ለግል ጉዳይ የሚጓዙትን እንደሆነ በግልጽ አያስረዳም ሲል…
Read More