Teffmilk

ኢትዮጵያ ከጤፍ የተሰራ የወተት ምርትን ለዓለም ገበያ አስተዋወቀች

ኢትዮጵያ ከጤፍ የተሰራ የወተት ምርትን ለዓለም ገበያ አስተዋወቀች

ኦሪጅናል ቴፍ-ሊ የተባለው ከጤፍ የተሰራ የወተት ምርት ዛሬ በለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በአምራቾቹ ትብብር በተዘጋጀ የማስተዋወቂያ መድረክ ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡ በዝግጅቱ ላይ ከንግድ ማህበረሰቡ፣ ከሚዲያ፣ ከእንስሳት ተዋጽኦዎች ነፃ በሆኑ ምግቦች ምርት እና ግብይት ውስጥ የሚሳተፉ ኢንዱስትሪዎች አባላት እና የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከእፅዋት የተዘጋጁ የምግብ አማራጮች ፍላጎት እየጨመረ መምጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ዝግጅቱ ጤፍን ለአለም አቀፍ ታዳሚዎች የበለጠ ለማስተዋወቅ እድል ፈጥሯል። በብሪታንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብሩክ መኮንን በመክፈቻ ንግግራቸው ጤፍ በኢትዮጵያዊያን የአመጋገብ ዘይቤ ውስጥ ያለውን ሰፊ ቦታ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም በሚችሉ የምግብ ስርዓቶች ጥናቶች ላይ ሊያበረክት ስለሚችለው አዎንታዊ አስተዋጽኦ አብራርተዋል፡፡ የኦሪጅናል ቴፍ-ሊ (The Original Teff-ly) መስራቾች…
Read More