Tamrattola

ኢትዮጵያ በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

ኢትዮጵያ በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በየ አራት አመቱ አንዴ የሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር በፓሪስ ሲካሄድ 15ኛ ቀኑን ይዟል። 206 ሀገራት በሚሳተፉበት በዘንድሮው ውድድር ከ10 ሺህ 500 በላይ አትሌቶችም እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡ ዛሬ ረፋድ በተካሄደው የወንዶች ማራቶን ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ ርቀቱን በ2:06:26 በሆነ ሰዓት አሸንፏል፡፡ አትሌት ታምራት ቶላ ውድድሩን የጨረሰበት ሰዓት አዲስ የኦሎምፒክ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ እንዳሸነፈም ተገልጿል፡፡ ውድድሩን ቤልጂየማዊው በሽር አብዲ ሁለተኛ እንዲሁም ኬንያዊው ቤንሰን ኪፕሩቶ ደግሞ ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡ አትሌት ታምራት ቶላ ከውድድሩ በኋላ እንዳለው "ውድድሩን በማሸነፌ እና የወርቅ ሜዳልያውን ለሀገሬ ኢትዮጵያ በማስገኘቴ በጣም በጣም ተደስቻለሁ" ሲል በእምባ ታጅቦ አስተያየቱን ሰጥቷል። አትሌት ታምራት ቶላ በውድድሩ በ2:06:26 በሆነ ሰዓት በመግባት በወንዶች ማራቶን የኦሎምፒክ ሪከርድ ባለቤት መሆን…
Read More