20
Feb
ኢትዮጵያ በሰለጠነ የሰው ሀይል ዕጥረት ምክንያት ሰራተኞችን ወደ ውጭ ሀገራት መላክ እንዳልቻለች ተገለጸ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በዘረጋው የውጪ ሀገር የሥራ ስምሪት ገበያ ላይ ሂዶ ለመስራት ከሀገራት ከሚቀርበው ጥያቄ አንፃር፤ በከፍተኛ ሁኔታ የሚላኩ ዜጎች እጥረት መኖሩን ገልጿል፡፡ ከመዳረሻ ሀገራት በኩል በርካታ የሰለጠነ የሰው ሀይል ጥያቄን ለኢትዮጵያ እንደሚቀርብ የገለጹት፤ በሚኒስቴሩ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ፕሮጀክት ፅ/ቤት ኃላፊ ብርሀኑ አለቃ ናቸው፡፡ በብዛት የሰው ሀይል ጥያቄ ያለባቸው ሀገራት በሙሉ ከኢትዮጵያ ሰው ለመውሰድ ፍላጎት እንዳላቸውም ሀላፊው አንስተዋል። ጥያቄ ከሚያቀርቡ ሀገራት መካከልም ከመካከለኛው ምስራቅ ኳታር፣ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ኩዌት፣ ሊባኖስ እና ጆርዳን ናቸው። እንዲሁም ከአውሮፓ ሀገራት ደግሞ ጀርመን፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ እና ፖላንድ በከፍተኛ…