23
Jul
በካሙዙ ካሳ የተቋቋመው ሻኩራ ፕሮዳክሽን የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋወቅ ከቻይና አምባሳደር ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። በቤጂንግ ከተማ የተፈረመው ይህ ስምምነት የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋወቅ ወደ ቤጂንግ ያቀናው "ኢትዮ ኪን" ባህል ቡድን አንድ አካል ነው። በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ተቋማት የኢትዮጵያን እና ቻይናን ባህል፣ ኪነ ጥበብ፣ ትምህርት እና ሌሎች የመልካም ገጽታ ማስተዋወቅ ስራዎችን በጋራ ይሰራሉ ተብሏል። የቻይናው የባህል እና ሚዲያ አገናኝ ኩባንያ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሚንግዙ ዛንግ በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት "የአባይ ወንዝ መገኛ፣ ቡና መገኛ፣ ታላቅ ህዝብ እና ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ ባህል ለማስተዋወቅ እንፈልጋለን" ብለዋል። "የቻይና ባህል ባለፈው ታሪክ ላይ ብቻ የተመሰረተ አይደለም" ያሉት ፕሬዝዳንቱ ከፈጠራ ጋርም እንደሚያያዝ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም በቀጣይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ…