Samesex

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን እንደማትፈቀድ አስታወቀች

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን እንደማትፈቀድ አስታወቀች

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ባሳለፍነው ሰኞ የቤተ-ክርስትያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቃድ መስጠታቸው ይታወሳል። ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ አዲሱን የቫቲካን መመሪያ የሚያትቱ መዛግብትን ማፀድቃቸውን ተከትሎ ነበር የቤተ-ክርስትያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቃድ መስጠታቸው የተሰማው። ፖፕ ፍራንሲስ፤ የቤተ-ክርስትያኒቱ ቄሶች የተመሳሳይ ፆታ “ያልተለመዱ” ጥንዶችን በአንዳንድ ሁኔታዎች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቅጃለሁ ሲሉ ተሰምተዋል። ቫቲካን ይህንን ተከትሎ በሰጠው ማብራሪያ ይህ የሚሆነው በተለምዶ በቤተክርስትያኗ በሚካሄዱ ሥነ-ሥርዓቶች ላይ እንዳልሆነ እና አሁንም ቢሆን ትዳር በአንድ ወንድና ሴት መካከል የሚደረግ ሥነ-ሥርዓት እንደሆነ ነው የምናየው ብሏል። የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ፤ የሊቀ ጳጳሱ መልዕክት…
Read More