10
Nov
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ ለመንግስታዊው የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ጋዜጣ ፕላስ ክፍል በሰጡት ቃል "በኢትዮጵያ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ክፍት የመንግሥት የሥራ መደቦች ባሉበት ሁኔታ ምንም ዓይነት ሠራተኞችን የመቀነስ ዕቅድ የለም " ሲሉ ገልጸዋል። በፌዴራልና በክልል ደረጃ የመንግሥት የሥራ መደቦችን የመረጃ የማጥራትና የማደራጀት ሥራ በተግባር መከናወኑንና ከ6 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የሥራ መደቦች መኖራቸው መለየቱን ገልጸዋል። ከእነዚህ ወደ 2 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚጠጉት በሠራተኞች የተያዙ ሲሆን፤ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ከፍት የሥራ መደቦች ይገኛሉ ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ የስራ መደቦችን የማጠፍ ዓላማ እንዳልተያዘም ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። "ኢትዮጵያ ካላት እያደገ ከመጣ የሕዝብ ብዛትና የአገልግሎት ፍላጎት አንጻር ተጨማሪ የመንግሥት…