16
Jan
ሜልፋን ቴክ በተሰኘ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ኩባንያ የተሰራው ሞል ኢን አዲስ መተግበሪያ በወጣት ኢትዮጵያዊያን የተሰራ ነው። የመልፋን ቴክኖሎጂ ስራ አስኪያጅ አቶ መልካሙ ምትኩ በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት መተግበሪያው ፈጣን እና የእለት ተዕለት ህይወታችንን በማቅለል ረገድ ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል። መልፋን ቴክ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ ከአምስት አመታት በላይ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ከፌደራልና ከክልል አስተዳደሮች፣ ከግልና አንጋፋ ከሆኑ የአገሪቱ ተቋማት ጋር በርካታ ስራዎችን ሲሰራም ቆይቷል ብለዋል። የተለያዩ የሶፍትዌር ስራዎችን፣ የሞባይልና የኮምፒውተር አፕልኬሽኖችን፣ የተቋማትን ሲስተም ማበልፀግን እና ለዲጂታል ኢትዮጵያ እቅድ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል። መልፋን ቴክ ከ45 በላይ ለሚሆኑ ባለሙያዎች የስራ ዕድል ፈጥሮ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ድርጅቶች በደንበኝነት አፍርቶ፣ ከ14…