13
Nov
በሽታው ላለፉት ተከታታይ ሶስት አመታት ከጨመረ በኋላ በከፍተኛ መጠን ቀንሶ እንደነበር ከሰሞኑ በሆሳዕና በተካሄደ የ2018 ዓመታዊ የጤና ዘርፍ የግምገማ መድረክ የገለጹት ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበጀት ዓመቱ 6 ነጥብ 8 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች በወባ መያዛቸውን ተናግረዋል። ቁጥሩ በ2017 ከነበረው በ37 በመቶ ቀንሷል ያሉት ሚኒስትሯ በባለፉት 3 አመታት ከነበረው በእጥፍ እጥፍ መቀነስ መቻሉንና በወባ ምክንያት የሚሞቱ ወገኖች ቁጥርም ከነበረበት ከ50% በላይ ስለመቀነሱ ገልጸዋል። ሆኖም “በአመቱ ከ6 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎቻችን ዛሬም በወባ በመያዛቸው ትንሽ ቁጥር የማንለው መሆኑ ሊታወቅ ይገባል” ያሉት ሚኒስትሯ በወባ ምክንያት የሚያጋጥመው ሞት ከድሮው አንጻር አነስተኛ ቢሆንም በዓመቱ ውስጥ 378 ሞቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል። ዶ/ር መቅደስ ዛሬም በ134…