21
Aug
የአፍሪካ ቁጥር አንድ ቢሊኒየር ናይጀሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ በኬንያ ላሙ አካባቢ ለመገንባት ላቀዱትና በቀን 700,000 በርመል ነዳጅ የማጣራት አቅም የሚኖረው ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ማቀዱ ይታወሳል። ይህ ፕሮጀክት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የ30 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ እንዲገዙ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ኢትዮጵያ የተወሰነ ድርሻ የመግዛት ፍላጎት እንዳላት ተገልጿል። የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ የኢኮኖሚ አማካሪ ዴቪድ ንዲ በናይሮቢ በተካሄደ የካፒታል ማርኬት መድረክ ላይ ይህንን የኢትዮጵያ ፍላጎት ይፋ ማድረጋቸውን እንደሆነ ብሉምበርግ ዘግቧል። አማካሪው ከዚህ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የ30 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ መቅረቡን ገልጸዋል። አማካሪው አክለውም፥ ኬንያ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውን የ10 በመቶ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት ማሳየቷንና ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳም በፕሮጀክቱ…