Jinka

ኢትዮጵያ ሶስት ዜጎቿ በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን ገለጸች

ኢትዮጵያ ሶስት ዜጎቿ በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን ገለጸች

በአሁኑ ሰዓት በማርበርግ ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ በሕይወት ያለ ሰዉ አለመኖሩን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። እስካሁን ድረስ የሶስት ሰዎች ህይወት በማርበርግ ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸዉን ማጣታቸውንም ሚኒስቴሩ ጠቅሷል። ጤና ሚኒስቴር የማርበርግ በሽታ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እንደገለጹት ሚኒስቴሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ የማርበርግ በሽታ መከሰቱን ካሳወቀበት ህዳር 3 ጀምሮ የበሽታዉ ምልክት ያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸዉ የተባሉ ሰዎችን ቦታዎች ላይ የመለየት ስራ እየሰራ ይገኛል። ሚኒስቴሩ እስካሁን ድረስ 17 የላብራቶሪ ናሙና ወስዶ የመረመረ ሲሆን፤ በሶስት ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ ስድስት ሰዎች የበሽታዉን ምልክት አሳይተዉ ህይወታቸዉ ቢያልፍም በላብራቶሪ የተረጋገጠዉ ግን ሶስት ሰዎች ላይ መሆኑን…
Read More