Insurancelaw

ብሔራዊ ባንክ የኢንሹራንስ ባለአክሲዮኖችን ለመመዘን አዲስ መመሪያ አወጣ

ብሔራዊ ባንክ የኢንሹራንስ ባለአክሲዮኖችን ለመመዘን አዲስ መመሪያ አወጣ

ብሔራዊ ባንክ ያወጣው አዲስ መመሪያ በኢንሹራንስ ዘርፉ ላይ ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን እና የተጠናከረ የኮርፖሬት አስተዳደርን ለማስፈን ያለመ ነው ብሏል። በዚህ መመሪያ መሠረትም ማንኛውም የኢንሹራንስ ኩባንያ የቦርድ አባላት ስብጥር አንድን ጾታ ብቻ የያዘ መሆን የለበትም። እያንዳንዱ የኢንሹራንስ ኩባንያ ቢያንስ ሁለት ሴት የቦርድ አባላት ሊኖሩት እንደሚገባ መመሪያው የግዴታ መስፈርትን አስቀምጧል። በተጨማሪም አንድ የቦርድ አባል ለመሆን ዝቅተኛው የዕድሜ ገደብ 30 ዓመት መሆን እንዳለበት ተደንግጓል። እያንዳንዱ የኢንሹራንስ ኩባንያ ሦስት ገለልተኛ የቦርድ አባላት ሊኖሩት ይገባል የተባለ ሲሆን እነዚህ ግለሰቦች የሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው እና በፋይናንስ ዘርፍ ወይም ተያያዥ መስኮች የ10 ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል ተብሏል። እንደ መመሪያው ከሆነ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች በገለልተኛ የቦርድ…
Read More