ICAO

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት አባልነት ብቸኛዋ የአፍሪካ ዕጩ ሆነች

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት አባልነት ብቸኛዋ የአፍሪካ ዕጩ ሆነች

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ምክር ቤት አባልነት አፍሪካን በመወከል ብቸኛ ዕጩ መሆኗ የውጩ ጉዳይ ሚኒስቴር ኣስታውቋል፡፡ ሚኒቴሩ እንዳለው እጩነቱ ሀገሪቱ ለዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ዘርፍ የምታደርገውን አስተዋፅኦ እና የአፍሪካን ጥቅም በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን መድረክ ለማስከበር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን መስራች አባል እንደመሆኗ ባለፉት በርካታ አሥርት ዓመታት ያካበተችውን ተቋማዊ ልምድ፣ የቴክኒክ ብቃት እንዲሁም በአቪዬሽን ደህንነት፣ ጥበቃና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ያላትን ጠንካራ ስም ይዛ ለምክር ቤት አባልነቱ መቅረቧን አመልክቷል። አፍሪካን ከአውሮፓ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከእሲያ ጋር የሚያገናኝ ስልታዊ የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ያላት ኢትዮጵያ በሰፊ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎቷ፣ በዘመናዊ የአቪዬሽን ሥልጠና፣ በጥገና እንዲሁም በካርጎ አገልግሎት አቅሟ…
Read More