06
Oct
መደበኛ ባልሆነ እና በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር የሚፈልሱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በማያውቁት ሀገር ለውትድርና እየተመለመሉ ነው ሲሉ በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ሁሪያ አሊ ተናግረዋል። በተጨማሪም ሕገ-ወጥ ፍልሰተኞቹ ከሚያጋጥሟቸው የከፉ ችግሮች መካከል፤ እሥር፣ የወሲብ ባርነት፣ መደፈር፣ ከባድ አካላዊ ቅጣት፣ አካል ጉዳተኝነት፣ እንደ ኩላሊት ያሉ የውስጥ አካልን በግዳጅ መዘረፍ እንደሚገኙበት ገልጸዋል። ይሁንና ሚንስትሯ ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ለየትኛው ሀገር በውትድርና እንደተመለመሉ አልጠቀሱም። ኢ-መደበኛ በሆነ መንገድ ከሀገር የሚወጡት ዜጎች ከአካል ጉዳት እና የግዳጅ ውትድርና በተጨማሪ፤ ለአዕምሮ ጤና እክል እና ለሥነ-ልቦና ቀውስ ተጋላጭ እንደሚሆኑም ተነስቷል። ሚኒስትር ደኤታዋ አያይዘውም፤ የሰው ልጅ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማኅበራዊ ፍላጎቶችን ለማጣጣም ከቦታ ቦታ መንቀሳቀሱ ግድ ቢሆንም፤ እንቅስቃሴው ሕጋዊ መስመርን…