07
Oct
በኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን በፋይናንስ ለመደገፍ 'ኢንተርፕርነርሺፕ ኢንቨስትመንት ባንክ' ሊቋቋም መሆኑ ተገልጿል። ባንኩ በ20 ሚሊዮን ዶላር መነሻ ካፒታል የሚመሰረት ሲሆን፣ ወጣቶች ለድጋፍ የሚያስይዙት ዋስትና የፈጠራ ሀሳባቸውን ብቻ እንደሚሆን ተጠቁሟል። ባንኩን ለማቋቋም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ ፊርማ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ተቋሙ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለኢንተርፕራይዞች አቅም መጎልበት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል። ይህ እርምጃ መንግስት የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያወጣቸውን ፖሊሲዎች ወደ ተግባር የመቀየር አካል መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ገልጸው፣ ባንኩ የወጣቶችን ጥያቄ በመመለስ የፈጠራ አቅማቸውን ለማጎልበት ያስችላል ብለዋል። ከመነሻ ካፒታሉ 10 ሚሊዮን ዶላር ከአፍሪካ ልማት ባንክ በድጋፍ…