12
Jul
በኢትዮጲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት የመንጃ ፍቃድ ስልጠና መስጠት ተጀመረ አሁን ላይ 22 ታራሚዎች ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛል ተብሏል፡፡ የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽነር ጀኔራል ዳመና ዳሮታ እንዳሉት ለመጀመሪያ ጊዜ በዝዋይ ማረሚያ ማዕከል ለታራሚዎች የአሽከርካሪ መንጃ ፍቃድ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡ ስልጠናው በማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ታሪክ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ማእከል የመጀመሪያው ሲሆን ታራሚዎች የእርምት ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ በቀጥታ ወደ ስራ አለም እንዲገቡ የሚያግዝ ነው ተብሏል። ለመጀመሪያ ጊዜ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ማእከል ሲከፍት ለታራሚው እና ለፖሊስ አባላት እንዲያገለግል ታስቦ ሲሆን እስካሁን 22 ታራሚዎች ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛል። የህግ ታራሚዎችን በይበልጥ የሙያ ባለቤት የማድረግ ስራ በቀጣይ በማስፋፋት ከመንጃ ፍቃድ በተጨማሪ የመካኒክነት ስልጠናና የተሽከርካሪ…