22
Nov
ያንጎ ኢትዮጵያ፣ የመንገድ ደኅንነት ሥልጠና እና የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ዕውቅና መስጠት ጀመረ የዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ ያንጎ ግሩፕ አካል የሆነውና በጂቱጂ አይቲ ሶሊውሽን አ.ማ. እና በኤለጋንስ ኢምፖርት ኤንድ ኤክስፖርት ፒኤልሲ ሥር የሚተዳደረው ያንጎ ኢትዮጵያ፣ ለደኅንነት፣ ለአገልግሎት ልህቀት እና ቅልጥፍና እንዲሁም ለማኅበረሰብ ተሳትፎ ያለውንቁርጠኝነት በማጠናከር የመንገድ ደኅንነት ፕሮግራም እና የመጀመሪያ እርዳታ እና የአገልግሎት ልህቀት ሥልጠና መርሐግብር ለአጋር አሽከርካሪዎች መስጠት ጀምሯል፡፡ “ያንጎ ኬርስ” በተሰኘው የማኅበራዊ ድጋፍ አገልግሎት ስር የተጀመረው ይህ ተነሣሽነት፣ የኩባንያው ትኩረት ይበልጥ ደኅንነታቸው በተጠበቁ መንገዶች፣ በጠንካራ ማኅበረሰቦች እናለተሳፋሪዎች ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ያሳያል፡፡ የሥልጠናው ክፍለ ጊዜ፣ አጋር አሽከርካሪዎች የመንገድ ደኅንነት ግንዛቤ እና ተግባራዊ የመጀመሪያ ህክምና ክህሎቶችን እንዲታጠቁ በማድረግና…