Bustransport

ከአዲስ አበባ-ሀርጌሳ- ጅቡቲ የአውቶቡስ ትራንስፖርት ሊጀመር ነው

ከአዲስ አበባ-ሀርጌሳ- ጅቡቲ የአውቶቡስ ትራንስፖርት ሊጀመር ነው

ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ ወራት ወደ ሶማሊላንድ እና ጅቡቲ የአውቶቡስ ትራንስፖርት አገልግሎት የማስጀመር እቅድ እንዳላት ገልጻለች። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ባረኦ ሀሰን መቀመጫውን ኬኒያ ናይሮቢ ያደረገው አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች ባለቤት እና ማኔጅመንት አባላት ጋር ተወያይተዋል። አቶ በሪኦ በዚህ ጊዜ እንዳሉት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚንስቴር በተያዘው በጀት አመት ኬኒያ፣ ጅቡቲ እና ሶማሌላንድ በየብስ ትራንስፖርት ለማገናኘት እቅድ መያዙን ገልጸዋል። አገልግሎቱን የመንግስትና ግሉን ዘርፍ ትብብር በማጠናከር በጋራ እንደሚሰራም ሚንስቴር ዴዔታው ተናግረዋል። በመሆኑም እንደሚኒስቴር መስሪያቤት በሁለቱ ሀገራት በትብብር ለመስራት አስፈላጊ የሆኑ የህግ ማዕቀፎችን የማመቻቸቱን ስራ በትኩረት እንደሚሰራ እና በድርጅቱ በኩል አስፈላጊውን ሂደት አሟልተው እንዲመጡ ከስምምነት መደረሱን ሚንስቴሩ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ያወጣው መግለጫ ያስረዳል። የአቢሲኒያ ሌግዠሪ…
Read More