Bobmenedez

አሜሪካዊው ፖለቲከኛ ቦብ ሜንድዝ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ መቀበላቸው ተረጋገጠ

አሜሪካዊው ፖለቲከኛ ቦብ ሜንድዝ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብጽ ጉቦ መቀበላቸው ተረጋገጠ

ቦብ ሜንድዝ ባለፉት 40 ዓመታት ውስጥ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ የሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው፡፡ የዘር ሀረጋቸው ከኩባ የሚመዘዘው ሜንድዝ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤትን ከመቀላቀላቸው በፊት የኒው ጀርሲዋን ዩኒየን ሲቲን በከንቲባነት አገልግለዋል፡፡ እኝህ ጉምቱ ፖለቲከኛ በፈረንጆቹ 2020 ላይ የወቅቱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አድርገዋል ተብሏል፡፡ እንደ አሜሪካ ድምጽ ዘገባ ከሆነ ፖለቲከኛው ይህን ያደረጉት ከግብጽ ባለስልጣናት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ጉቦ ከተቀበሉ በኋላ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ…
Read More