27
Jun
ወደብ አልባ የሆነችው የኢትዮጵያ መከላከያ ዋና አዘዥ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፈጣን ተዋጊ ጀልባዎችን ጎብኝተዋል፡፡ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአየር ኃይል አቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከል ወደ አገልግሎት የመለሳቸውን ፈጣን ተዋጊ ጀልባዎችን እንደጎበኙ የሀገር መካለከያ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል። ተዋጊ ጀልባዎቹ በቀድሞ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አገልግሎት የሠጡ ሲሆን ዳግም የባሕር ኃይሉን ዝግጁነት ያጠናክራሉም ተብሏል። የአየር ኃይል አቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከል ከ30 አመት በላይ ተገለው እና አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ጀልባዎችን የፈጣን ተዋጊ ጀልባ ቴክኖሎጂ እና መሳሪያዎች በመግጠም ለግዳጅ ዝግጁ መደረጋቸውም ተገልጿል። ኢትዮጵያ የባህር ሀይልን እንዳዲስ በማደራጀት ላይ መሆኗን ከሁለት ዓመት በፊት መግለጿ ይታወሳል፡፡ የቀድሞ የኢትዮጵያ አካል የሆነችው ኤርትራ…