የአውሮፓ ሕብረት ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ደህንነት መስፈርቶችን አያሟሉም ባላቸው በ12 የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች ላይ ጥብቅ የበረራ እገዳ ጥሏል።
እንደ ሬውተርስ ዘገባ ከሆነ ለእገዳው ዋና ምክንያት በየሀገራቱ የሚገኙ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣናት በአየር መንገዶቻቸው ላይ የሚያደርጉት የቴክኒክና የደህንነት ቁጥጥር ከዓለም አቀፉ ስታንዳርድ በታች መሆኑ ነው።
በዚህ አዲስ ውሳኔ መሠረት በጥቁር መዝገብ ውስጥ የገቡ አየር መንገዶች አጠቃላይ ቁጥር 87 የደረሰ ሲሆን፣ የተካተቱት ተቋማት ወደ ማንኛውም የአውሮፓ ሕብረት አባል ሀገር መብረርም ሆነ የአየር ክልሉን መጠቀም ፈጽሞ አይችሉም።
በዚህ የደህንነት ጥቁር መዝገብ ውስጥ በእገዳው የተጠቃለሉት 12ቱ የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች አንጎላ፣ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ጅቡቲ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኤርትራ፣ ላይቤሪያ፣ ሊቢያ፣ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ፣ ሴራሊዮን፣ ሱዳን እና ታንዛኒያ መሆናቸው ተረጋግጧል።
እነዚህ ሀገራት በአቪዬሽን ዘርፋቸው ላይ በቂ የቁጥጥር ማሻሻያዎችን እስኪያደርጉ ድረስ እገዳው የሚቀጥል ሲሆን፣ የሕብረቱ የአየር ደህንነት ዝርዝር መረጃ የመንገደኞችን ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል በየጊዜው እንደሚከለስ ተገልጿል።
ከምስራቅ አፍሪካ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን እና ታንዛኒያ የተመዘገቡ አየር መንገዶች ወደ ግዛቴ እንዳይገቡ ሲል እገዳ ጥሏል፡፡
ተቋሙ እገዳውን የጣለው ከተጠቀሱት ሀገራት የሚነሱ አየር መንገዶች የመንገደኞችን ደህነንት ማስጠበቅ የሚያስችል ብቃት የላቸውም በሚል ነው፡፡
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በ2025 ዓመት በዓለም ላይ 429 ሰዎች በአውሮፕላን አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን እንዳጡም ገልጿል፡፡
በአውሮፕላን አደጋዎች የሚሞቱ ዜጎችን ቁጥር ለመቀነስ በየዓመቱ የአቪዬሽን ሪፖርት ይፋ ደርጋል፡፡