ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ምክር ቤት አባልነት አፍሪካን በመወከል ብቸኛ ዕጩ መሆኗ የውጩ ጉዳይ ሚኒስቴር ኣስታውቋል፡፡
ሚኒቴሩ እንዳለው እጩነቱ ሀገሪቱ ለዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ዘርፍ የምታደርገውን አስተዋፅኦ እና የአፍሪካን ጥቅም በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን መድረክ ለማስከበር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሲቪል አቪዬሽን ኮሚሽን መስራች አባል እንደመሆኗ ባለፉት በርካታ አሥርት ዓመታት ያካበተችውን ተቋማዊ ልምድ፣ የቴክኒክ ብቃት እንዲሁም በአቪዬሽን ደህንነት፣ ጥበቃና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ያላትን ጠንካራ ስም ይዛ ለምክር ቤት አባልነቱ መቅረቧን አመልክቷል።
አፍሪካን ከአውሮፓ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከእሲያ ጋር የሚያገናኝ ስልታዊ የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ያላት ኢትዮጵያ በሰፊ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎቷ፣ በዘመናዊ የአቪዬሽን ሥልጠና፣ በጥገና እንዲሁም በካርጎ አገልግሎት አቅሟ የዓለም አቀፍ ትስስርን ማጠናከሯን ቀጥላለች ተብሏል።
ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ አባል ሆና ስትመረጥ የድርጅቱን ዓላማዎች ለማሳካት፣ ይበልጥ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ አቪዬሽንን ለማስፋፋት፣ ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር ሀገራት ከዘላቂ የአቪዬሽን ዕድገት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለመሥራት ቃል መግባቷን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ ሎሎች የአቪዬሽን ተቋማት በየዓመቱ አፍሪካዊያን የአቪዬሽን ባለሙያዎችን በተለይም ቴክኒሺያኖች፣ የበረራ ባለሙያዎች፣ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና ሌሎች ሌሎች ባለሙያዎችን በማሰልጠን ላይ ትገኛለች።
ከስልጠና በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ55 በላይ ወደሆኑ የአፍሪካ አየር መንገዶች በመብረር ላይ ይገኛል።