አሜሪካ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከከፋ ግጭት እንዲታቀቡ አሳሰበች

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርክ ሩቢዮ እንዳሉት በኢትዮጵያ ላይ የድሮን ጥቃቶች መሰንዘራቸውን ኮንነው በታጣቂዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ መሆኗን ገልጸዋል።

ታጣቂዎቹ በድሮን ጭምር የታገዘ ጥቃት መክፈታቸውን እና አሜሪካ የታጣቂዎቹን ድርጊትን ሩቢዮ አውግዘዋል።

አሁን ላይም የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦር በጋራ ድንበሮች አካባቢ ከፍተኛ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ መሆናቸውንም ሩቢዮ አክለዋል።

ዓለማችን እና ምስራቅ አፍሪካ ተጨማሪ ጦርነት የማስተናገድ አቅም የለውም ያሉት ሚንስትሩ ኢትዮጵያ እና ኤርትራም ራሳቸውን ከግጭት ማራቅ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የፌደራል መንግሥት በህወሀት እና አጋሮቹ የደረሰበትን ጥቃት በመመከት ላይ ሲሆን የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌን ጨምሮ ሁሉንም የዞን ከተሞች መቆጣጠሩ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያን ግዛት አልፈው በገቡ በኤርትራ ጦር ላይ የድሮን ጥቃቶችን መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በስፋት ተሰራጭተዋል።

አሜሪካ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ላይ ጥላባቸው የነበሩ አነስተኛ ማዕቀቦችን ማንሳቷን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፣ ይህም ውሳኔ ከሁለቱም ወገኖች ጋር የመነጋገር እድልን በማስፋት የሰላም አስማሚነት ሚናዋን ለመወጣት የታለመ መሆኑን አስረድተዋል።

በቀጠናው ያለውን አለመረጋጋት ለመቀነስ አሜሪካ ከኢትዮጵያ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጓን የገለጹት ማርኮ ሩቢዮ፣ ሁኔታውን በትዕግስትና በሰከነ መንገድ እንዲመሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ገልፀዋል።

አያይዘውም፣ አሁን ያለው ሁኔታ ሌሎች አገራትን ወደ ጦርነት የሚስብ ሰፊ ቀጠናዊ ግጭት እንዳይፈጥር ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ እና አሁን ላይ አለም ተጨማሪ ጦርነት እንደማያስፈልጋት አሳስበዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *