565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ወደ ዩንቨርስቲ አላስገቡም ተባለ

በዘንድሮው ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 565 ያህሉ አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸው ተገልጻል።

ዘንድሮ በ2018 ብሔራዊ ፈተና የተመዘገበው ተማሪ ቁጥር 563,960 ሲሆን  550,210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።

ከተፈተኑት ውስጥም 12 በመቶ ወይም 70 ሺህ 544 ተማሪዎች ብቻ ወደ ዩንቨርስቲ የሚያስገባቸውን ውጤት አስመዝግበዋል ተብሏል።

ከተፈጥሮ ሳይንስ 16.6 በመቶ እንዲሁም ከማህበራዊ ሳንይስ 8.3 በመቶ ያህሉ ማለፋቸውን የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል።

አዲስ አበባ ካስፈትናቸው ተማሪዎች ውስጥ 32.3 በመቶዎቹ ሲያልፉ፣ ሀረሪ 22.67%፣ አፋር 15.6%፣ አማራ 15.56%፣ ድሬዳዋ 11.29፣፣ ትግራይ 11.2%፣ ኦሮሚያ 10.5 በመቶ አሳልፈዋል።

ባለፉት ዓመታት ዋነኛ የግጭት እና ጦርነት ቀጠና በሆኑት በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ክልል ያለፉ ተማሪዎችን ስንመለከትም በኦሮሚያ 20 ሺህ 807 ተማሪዎች ሲያልፉ
በአማራ ክልል 15 ሺህ 225 ተማሪዎች እንዲሁም በትግራይ ክልል  3 ሺህ 146 ተማሪዎች ወደ ዩንቨርስቲ የሚያስገባቸውን ውጤት አስመዝግበዋል።

ባለፈው ዓመት ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች ቁጥር 1 ሺህ 232 የነበሩ ሲሆን ዘንድሮ ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ወደ 565 ዝቅ ማለቱ ተገልጿል።

በኦሮሚያ 156፣ በአማራ 98
እንዲሁም በትግራይ ክልል 48 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም ተብሏል።

በተጨማሪም ያስፈተኑትን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ባለፈው አመት 62 የነበሩ ሲሆን ዘንድሮ ወደ 88 ከፍ እንዳሉ ሚንስትሩ ገልጸዋል።

በኮምፕዩተር እና በወረቀት በተፈተኑ ተማሪዎች መካከል ያለው የማለፍ ምጣኔ ትልቅ ልዩነት አለው የተባለ ሲሆን ኦንላይን የተፈተኑ 18.3% ሲያልፉ በወረቀት የተፈተኑት የማለፍ ምጣኔያቸው ግን  4 ነጥብ 2% ብቻ ነው።

ከዘንድሮው ተፈታኞች ውስጥ 60 በመቶ ያህሉ በኦንላየን የተፈተኑ ናቸው ተብሏል።

የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤትን በሚመለከት በተፈጥሮ ሳይንስ በአዳማ ከተማ እሚገኘው ከወንድ 591/600 ኦዳ ስፔሻል ቦርንዲግ ትምህርት ቤት አዳማ ትልቁ ውጤት ሲሆን ከሴት ደግሞ በአማራ ክልል እንጅባራ ከተማ ያለው አገው ምድር ትምህርት ቤት 583/600 አምጥታለች።

በማህበራዊ ሳንይንስ ደግሞ ከወንድ በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው ዶዶላ ኢፋ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት  576/600 ሲመዘገብ ከሴት ደግሞ 569/600 አዲስ አበባ ቦሌ ሱፐርሆሊሴቪየር ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኗ ተገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *