የቻይናው ጓንዡ አውቶሞቢል ግሩፕ በኢትዮጵያ መኪና ማምረት እንዲጀምር ተጠየቀ

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ኩባንያው ከሽያጭ ማዕከል መክፈት በተጨማሪ የማምረቻ እና መገጣጠሚያ ማዕከልም እንዲከፍት ጠይቀዋል።

GAC JUNTU አዲስ ዘመናዊና ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠራ የትራንስፖርት ሥርዓት በማስተዋወቅ፣ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ቀዳሚ የኤግዚቢሽን ማዕከሉን በአዲስ አበባ በይፋ መርቋል።

የኩባንያው  የምርት ማሳየ 2,300 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው  ሲሆን ከማሳያነት ባለፈ  ከሽያጭ በኋላ  አገልግሎት፣  መለዋወጫ እና በአምራች የተደገፈ ዋስትና የሚሰጥበት አካቷል ተብሏል።

ተቋሙ የተሽከርካሪ ሽያጭን፣ የተረጋገጠ የድኅረ-ሽያጭ አገልግሎትን፣ ኦሪጅናል የመለዋወጫ ዕቃዎችን እና ከአምራቹ የሚሰጥ ዋስትናን ያካተተ የተሟላ የ4S-ደረጃ ሥርዓት (4S-standard ecosystem) በማቅረብ በኢትዮጵያ ለታማኝነትና ለደንበኞች አገልግሎት አዲስ መለኪያ ያስቀምጣል።

GAC JUNTU የኢትዮጵያን ገበያ  አራት ዘመናዊ  የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ይዞ መቅረቡን ጠቅሷል።

አራቱ ሞዴሎችም AION UT,AION V ,HYPTEC HT ,HYPTEC HL መሆናቸውን ሸገር ራዲዮ ዘግቧል።

ተሽከርካሪዎቹ ከፍተኛ አቅም ያላቸው ባትሪዎች የተገጠመላቸው እና ረጅም ርቀት  መጓዝ የሚያስችሉ፣ ባትሪያቸው የቻይናንና የአውሮፓን የ“አምስት ኮከብ” የደህንነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ናቸው ተብሏል።

GAC JUNTU የአዲስ አበባ የምርት ማሳያ እና ማዕከልን መርቀው የከፈቱት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ  የታዳሽ ሀይል የትራንስፖርት ስርዓትን ለመደገፍ በርካት እርምጃዎች ቀደም ብላ መውሰድ መጀመሯን አስረድተዋል።

የፖሊሲ ማሻሸያ ፣ማበረታቻዎች የመሳሰሉትን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

ኩባንያው የሽያጭ ማዕከል ከመክፈት ባለፈ የማምረቻ ወይንም የጥገና ማዕከል እንዲከፍት ሚንስትሩ አለሙ ስሜ  ጠይቀዋል።

GAC JUNTU የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት አስቦ እንዲሰራም አስረድተዋል።

የኩባንያው  የኢትዮጵያ ተወካይ በበኩላቸው
አስተማማኝነትን፣ ተደራሽነትን እና ፈጠራን ለማቅረብ የተነደፈ የተሟላ የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ሥርዓት (ecosystem) እያስተዋወቅን እንገኛለን” ብለዋል።

አላማቸውም ኢትዮጵያ ወደ ዘላቂ የትራንስፖርት አማራጭ የምታደርገውን ሽግግር መደገፍ ብለዋል።

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ይዞ የመጣው  GAC JUNTU  ከ86 በላይ ሀገራት እና ክልሎች ላይ እየሰራ እንደሆነ ተናግሯል።

1.5 ሚሊዮን ጠቅላላ የተሽከርካሪ ቁጥር ያላት በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ከታገዱ አንድ ዓመት አልፏቸዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *