ላዳው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ሌሎች የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ለመምከር ባደረጉት ጉዞ የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰንን አስከትለው አዲስ አበባ ገብተዋል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፎር ላንዳው እና የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን በኢትዮጵያ አየር ኃይል የተዘጋጀውን ዓለም አቀፍ የአቭዬሽን ኤክስፖ መጎብኘታቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ ከምስል ጋር አጋርቷል።
ኢትዮጵያ እና ግብጽን ጨምሮ አራት የአፍሪካ ሀገራትን በመጎብኘት ላይ ያሉት ክርስቶፈር ላንዳው በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ላንዳው በዛሬው ዕለት የተመሰረተበትን 90ኛ ዓመት እያከበረ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር ሀይል አቪዬሽን ኤክስፖ ጎብኝተዋል ተብሏል፡፡
ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ እና ግብጽ በተጨማሪ ኬንያ እና ጅቡቲን እንደሚጎበኙ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ በመገኘታቸው ክብር እንደሚሠማቸው እና ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጠል መናገራቸውም ተገልጿል፡፡
የአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን ለምስራቅ አፍሪካ ሰላም በተለይም እንደ አልሸባብ እና አይኤስኤስ ያሉ የሽብር ቡድኖን ለመከላከል እና ለመደምሰስ ከኢትዮጵያ ጋር እንደሚሰሩ መናገራቸው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ያጋራው ጽሁፍ ይገልጻል፡፡
የካይሮ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ የመጡት ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር “በቀጠናዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች” ላይ እንደሚወያዩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከሰሞኑ የሚኒስሩን ጉዞ አስመልክቶ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል።
ላንዳው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት እና ከግሉ ዘርፍ ተወካዮች ጋር በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ውይይት፤ ለዩናይትድ ስቴትስ “የንግድ ተሳትፎ የሚሆኑ ዕድሎችን ያስተዋውቃሉ” ተብሏል።
ላንዳው በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር የመገናኘት ዕቅድም ይዘዋል።
የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመጋቢት 2017 ዓ.ም የተሾሙት ክሪስቶፈር ላንዳው፤ ወደ ካይሮ እና አዲስ አበባ የሚጓዙት የሀገራቸው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያ እና ግብጽ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ምክንያት የገቡበትን ውዝግብ ለመፍታት እንደሚሹ ባስታወቁ በጥቂት ቀናት ውስጥ ነበር።
ላንዳው በነገው ዕለት ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ የሚጠበቅ ሲሆን ከአጀንዳዎቹ መካከልም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ እና ግብጽ የገቡበትን አለመግባባት ለመፍታት በሚል በዋሸንግተን ድርድር ማድረግ እንደሚሆን ይጠበቃል።