የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከኖርዌው የማዕድን ኩባንያ የ3 ሚ. ዶላር ድርሻ ገዛ

የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሀብት ፈንድ በአኮቦ የማዕድን ድርጅት የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ፈፀመ፡፡

የፈንዱ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ በኢትዮጵያ የወርቅ ማውጣት ሥራ ላይ ከተሠማራው የኖርዌው አኮቦ የማዕድን ኩባንያ  ሦስት ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው 7.4 በመቶ ድርሻ መግዛቱን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩክ ታዬ፤ “በአኮቦ ማዕድን የምናደርገው ኢንቨስትመንት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ መስፋፋት ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ እመርታ ነው” ብለዋል፡፡

ውሳኔው ኢትዮጵያ ከክፍለ ዘመን በኋላ ወደ ዓለም አቀፍ የአክስዮን ገበያ እንድትመለስ ያደረገና ለቀጣይ የድንበር ተሻጋሪ ኢንቨስትመንቶች በር የከፈተ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኢንቨስትመንቱ አኮቦ አዲስ ማዕድን ማውጫ ለመገንባት የሚያስፈልገውን ወጪ የሚደግፍ ሲሆን፤ ይህም የድርጅቱን ወርሃዊ የወርቅ ምርት ከ5-10 ኪሎ ግራም ወደ 50-80 ኪሎ ግራም ከፍ እንደሚያደርገው ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ ስምንት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የማዕድናት እና ቡና ንግድ ይሸፍናል።

ኢትዮጵያ ወርቅን ጨምሮ ከማዕድናት የምታገኘው ገቢ በየዓመቱ ከፍተኛ ጭማሪ በናሳየት ላይ ሲሆን አዳዲስ የማዕድን ኢንቨስትመንት ስምምነቶች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ።

የትግራይ ክልል ከፍተኛውን የወርቅ መጠን ለብሔራዊ ባንክ ያስገባ ሲሆን 189 ኩንታል ወርቅ ለባንኩ እንዳስገባ ተገልጿል።

በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ከትግራይ ክልል 189 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉን የትግራይ ክልል ማዕድን ቢሮ አስታውቋል።

የክልሉ ማዕድን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዓለም ሀድጉ እንደተናገሩት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት  189 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንከ በማስገባት ከ250 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱም ተገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *