ሻኩራ ፕሮዳክሽን የቻይና አምባሳደር ከተሰኘው ተቋም ጋር ስምምነት ፈጸመ

በካሙዙ ካሳ የተቋቋመው ሻኩራ ፕሮዳክሽን የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋወቅ ከቻይና አምባሳደር ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።

በቤጂንግ ከተማ የተፈረመው ይህ ስምምነት የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋወቅ ወደ ቤጂንግ ያቀናው “ኢትዮ ኪን” ባህል ቡድን አንድ አካል ነው።

በስምምነቱ መሰረት ሁለቱ ተቋማት የኢትዮጵያን እና ቻይናን ባህል፣ ኪነ ጥበብ፣ ትምህርት እና ሌሎች የመልካም ገጽታ ማስተዋወቅ ስራዎችን በጋራ ይሰራሉ ተብሏል።

የቻይናው የባህል እና ሚዲያ አገናኝ ኩባንያ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሚንግዙ ዛንግ በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት “የአባይ ወንዝ መገኛ፣ ቡና መገኛ፣ ታላቅ ህዝብ እና ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ ባህል ለማስተዋወቅ እንፈልጋለን” ብለዋል።

“የቻይና ባህል ባለፈው ታሪክ ላይ ብቻ የተመሰረተ አይደለም” ያሉት ፕሬዝዳንቱ ከፈጠራ ጋርም እንደሚያያዝ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም በቀጣይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የግል ህይወት ታሪክን የያዘ መጽሀፍ በሚቀጥለው ዓመት ይፋ እናደርጋለንም ብለዋል።

የሻኩራ ፕሮዳክሽን መስራች ካሙዙ ካሳ በበኩላቸው እያደገ ያለውን የኢትዮጵያ እና ቻይና ባህል ትስስር የበለጠ ማጎልበት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ባህል ልክ እንደ ቻይና በፈጠራ እና ኢንቨስትመንት የታጀበ እንዲሆን ፍላጎት እንዳላቸውም ካሙዙ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ኪን ዛሬ ምሽት ጀምሮ የሙዚቃ ስራዎቹን ለቻይናዊያን ማቅረብ እንደሚጀምርም ተገልጿል።

የባህልና ቱሪዝም ተወካይ ከፍያለው አብዲሳ በበኩላቸው የሁለቱ ተቋማት ስምምነት የኢትዮጵያን ባህል ለማሳደግ እንደሚጠቅም ተናግረዋል።

ከ2004 ጀምሮ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ለአድማጭ ተመልካቾች በማድረስ ላይ ያለው ሻኩራ ፕሮዳክሽን ከዚህ በፊት ከሻንጋይ ኦርኬስትራ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት እንደነበረቅም ተወካዩ ገልጸዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *