ኢትዮጵያ ለሙዚቀኞች የሮያሊቲ ክፍያ መክፈል ልትጀምር ነው

የሮያሊቲ ክፍያ ከመጪው ሐምሌ ወር ጀምሮ መክፈል ይጀመራል ተብሏል

የሙዚቀኞች የሮያለቲ ክፍያ ከሀምሌ ወር ጀምሮ መክፈል እንደሚጀመር ተገልጿል።

መገናኛ ብዙሀን ለሙዚቀኞች የሮያሊቲ ክፍያ እንዲከፍሉ የሚያስገደደው መመሪያ የፊታችን ሀምሌ 1ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

የሮያሊቲ ክፍያ ረቂቅ መመሪያው የሚመለከታቸው አካላትን ባሳተፈ መንገድ ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን  ህጉን ለማስፈጸም ስልጣን የተሰጠው የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ቢበዛ ከአምስት ወር በኃላ ፀድቆ ወደ ስራ እንደሚገባ የባለስልጣኑ ዋና ዳሬክተር አቶ ወልዱ ይመሰል ተናግረዋል።

በኢትዮጲያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን አማካኝነት የተሰናደው ይህ ውይይት፣ሙዚቀኞች፣ ፕሮዲውሰሮች፣ደራሲያን እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈውበታል።

ውይይቱ በዋናነት በሙዚቀኞች ሮያሊቲ ክፍያ ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ የክፍያ ቀመር  ተዘጋጅቷል።

የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር እና የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር በጋራ ያዘጋጁት ይህ የቀመር ሰነድ መገናኛ ብዙሀን ለሙዚቀኞች እንዴት መከፈል እንዳለባቸው ካስቀመጣቸው መስፈርቶች መካከልም፣ የመገናኛ ብዙሀኑን የገቢ ምንጭ የመለየት ስራዎችን በመስራት፣ መገናኛ ብዙሀኑ በቀን ወይንም በ24 ሰዓት ምን ያህል ሙዚቃ እንዳጫወቱ ማጣራት፣ EMCCMO.COM በተሰኘው ዌብ ሳይት በየመገናኛ ብዙሀኑ የሚተላለፍ ሙዚቃዎችን በመቁጠር (count) በማድረግ የክግያ ተመኑ ይሰላል ተብሏል።

እንዲሁም በሚዲያዎቹ የተላለፉ ሙዚቃዎች የስርጭት መጠንን በማጣራት እና የመሳሰሉት ዘዴዎችን በመጠቀም የሙዚቀኛው ስራ ምን ያህል አየር ላይ መዋሉ እና ሚዲያውም ምን ያህል መክፈል እንዳለበት እንደሚሰላ ተገልጿል።

ህይወታቸው ያለፈ ሙዚቀኞችን በሚመለከት የሟች  ወራሾች ገቢውን እንዲያገኙ የሚያደርገው ይህ መመሪያ ሌሎችንም ጉዳዮችንም አካቷል።

መመሪያው ተግባራዊ መሆን ሲጀምር  ሚዲያዎች  በአንድ ሙዚቃ በሚቀመጥላቸው የገንዘብ መጠን እና ጊዜ እንዲከፍሉ ያስገድዳል።

መገናኛ ብዙሀኑ ለሚያጫውቱት አንድ የሙዚቃ ስራ ምን ያህል ይክፈላሉ የሚለው እስካሁን ግልፅ ሆኖ አልተቀመጠም።

ኢትዮጵያ ከ1996 ዓ/ም ጀምሮ የአዕምሮ ፈጠራ ስራዎችን ጥቅም ለማስከበር ህግ ያወጣች ቢሆን በተለይም የሙዚቃ ባለሙያዎች ጥቅም ሳይከበር ቆይቷል፡፡

በ2007 ዓ/ም ደግሞ የአዕምሮ ስራ ውጤቶችን የበለጠ የሚያስከብር ነው የተባለ የተሻሻለ ህግ ያወጣች ቢሆንም ይህን ህግ መፈጸም እና መስፈጸም የሚያስችሉ መመሪያዎች ባለመውጣታቸው ምክንያት ህጉ እስካሁን መተግበር ሳይቻል ቆይቷል፡፡

የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅጂና ዘርፍ ማህበር የስራዎቻቸውን ጥቅም ለማስከበር ላለፉት 17 ዓመታት ሲታገል መቆየቱን አስታውቋል፡

የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅጂና ዘርፍ ማህበር ባዘጋጀነው የረቂቅ የሮያሊቲ ክፍያ ቀመር መሰረት ሙዚቃ አጫዋቾች እንዲከፍሉ የሚጠበቅባቸው በአንድ ሙዚቃ እስከ 20 ሳንቲም ድረስ ነው።

የክፍያ መንገዱም ሊያጫውቱት በሚችሉት የሙዚቃ መጠን ልክ ይሆናል፣ ከዓመታዊ ትርፋቸው ላይ እስከ 2 በመቶ፣ ክፍያቸውን ባጫወቱት ሙዚቃ ልክ አልያም የዓመት ፓኬጅ በመግዛት ሊሆንም ይችላል፣ እንደ ዲጄ እና መዝናኛ ቤቶች አይነት ደግሞ ከንግድ ፈቃዳቸው ጋር በማያያዝ እና በሚደረጉ ድርድሮች አማካኝነት ሊሆን ይችላል እንደሚችል ማህበሩ ከዚህ በፊት መግለጹ አይዘነጋም፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *