ኢትዮጵያ ስድስት የጭነት መርከቦችን ልትገዛ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ስድስት አዳዲስ የጭነት መርከቦችን ግዢ ሊፈፀም እንደሆነ አስታውቋል።

62 ሺህ ቶን የመጫን አቅም ያላቸው ሁለት አልትራማክስ የደረቅ ብትን ጭነት መርከቦች በአጭር ግዜ ተገዝተው አገልግሎት እንደሚጀምሩ ድርጅቱ ገልጿል፡፡

የቀሪ አራት መርከቦች ግዥ በቀጣዮቹ ዓመታት እንደሚፈፀም የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስን ጠቅሰው የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ኢትዮጵያ መርከቦቹን የምትገዛው የሀገሪቱን የገቢ ወጪ ንግድ እንቅስቃሴ ያግዛሉ በሚል ነው፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ላይ 10 መርከቦች እንዳሏት ይነገራል።

ከሁለት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ከ60 ሺህ ቶን በላይ እቃ የመጫን አቅም ያላትን መርከብ መረከቧ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በቅርቡ ባህር ዳር እና ሀዋሳ የተሰኙ ሁለት መርከቦች ለኪሳራ ዳርገውኛል በሚል መሸጡ ይታወሳል።

በተሸጡት ሁለት መርከቦች ምትክም አባይ የተሰኘች አዲስ መርከብ ከቻይና መግዛቱን በወቅቱ ተናግሮ ነበር።

አዲሷ መርከብም በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ታሪክ በግዙፍነቷ አቻ የላትም የተባለ ሲሆን መርከቧ በኢትዮጵያ እጅ መግባቷን ድርጅቱ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ድርጅት በ3 ሺህ ቶን የመጫን አቅም ባላቸው መርከቦች ስራውን መጀመሩ ይታወሳል።

በቻይናው ያንግዡ ዳያንግ ሺፕ ቢዩልዲንግ የተገነባችው ይህች መርከብ 200 ሜትር ርዝመት አላት የተባለ ሲሆን ይህችን መርከብ ለመግዛት ኢትዮጵያ ምን ያህል ገንዘብ ወጪ እንዳደረገች ድርጅቱ አልጠቀሰም።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *