2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና አዛን ውድድር ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት በዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርአን ማህበር አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን የማጠቃሊያ ውድድር በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል።

በማጠቃሊያ ውድድሩ በቁርዓን ሂፍዝ፣ በቁርዓን ቲላዋ እና በአዛን ዘርፍ አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች በዳኞች አማካኝነት ይፋ ሆነዋል።

በዚህም

በወንዶች የቁርአን ሂፍዝ ውድድር

1ኛ. ሙሐመድ ፉዓድ ከሊቢያ

2ኛ. ዩሱፍ አሺር … ከኳታር

3ኛ. አህመድ በሺር …ከአሜሪካ

በሴቶች የቁርአን ሂፍዝ ውድድር

1ኛ ሩቅያ ሳላህ … ከየመን

2ኛ ነሲም ጀናዉጃ … አልጄሪያ

3ኛ ቀመራ ወሊዩ መሐመድ … ከኢትዮጵያ

እንዲኁም በአዛን ውድድር

1ኛ ሙሀመድሻን አቡበከር … ከኢንዶኖዢያ

2ኛ ኡመር ዱራን … ከቱርክ

3ኛ አደም ጅብሪል … ከኢትዮጵያ

በወንዶች የቁርአን ቲላዋ ውድድር

1ኛ አብዱራዛቅ አል ሸሀዊ …ከግብፅ

2ኛ ከራር ለይስ … ከኢራቅ

3ኛ አንጀድ ካምዳን … ከየመን አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ከጥር 21 ቀን ጀምሮ እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው 2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርአን እና የአዛን ውድድር ላይ ከ60 በላይ ሀገራት ተሳትፈዋል ተብሏል።

በማጠቃሊያ ውድድሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኡለማዕ ጽህፈት ቤት፣ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች ስራ አስፈፃሚዎች፣ ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች መታደማቸውን የጠቅላይ ምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡

በውድድሩ ላይ ከ60 ሀገራት 100 ተወዳዳሪዎች እንዲሁም 11 ዳኞች ከሁሉም አህጉር ኢትዮጵያ የሚገቡ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆኑ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ የክብር እንግዶች የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ ተገኝተዋል፡፡

ይህ መድረክ ቱሪስቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመሣብ ቀላል የማይባል ሚና ተጫውቷል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የቁርዓን ውድድር ሲካሄድ የአሁኑ የመጀመሪያው ሳይሆን ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ውድድሮች በኢትዮጵያ እና በሌሎች ሀገራት ተካሂደዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *