የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ እየመሩ ገኛሉ፡፡
ትራምፕ እስካሁን በተረጋገጡ የወኪል መራጮች ምርጫ አማካኝነት 267 በ224 ድምጽ እየመሩ ይገኛሉ፡፡
አስቀድሞ 270 የወኪል መራጮችን ድምጽ ያገኘ እጩ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ይሆናል በሚለው ህግ መሰረት ዶናልድ ትራምፕ በይፋ ማሸነፋቸውን ለማወጅ ሶስት ድምጽ ብቻ መቅረቱን ተከትሎ በርካታ የዓለማችን ሀገራት አስቀድመው እንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን እያስተላለፉ ናቸው፡፡
ከነዚህ መካከልም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) አንዱ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን ስላሸነፉ እንኳን ደስ አለዎት፣ ወደ መሪነት እንኳን ድጋሚ መጡ አብረን እንደምንሰራ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው ለዶናልድ ትራምፕ እና ባለቤታቸው እንኳን ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ተመለሱ ሲሉ በኤክስ አካውንታቸው ላይ ጽፈዋል፡፡
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ኤልሳልቫዶር ፕሬዝዳንት ናይብ በክሌ፣ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ፣የሀንጋሪው ፕሬዝዳንት ኦርባን፣የስዊድን፣ ዴንማርክ ፣ጣልያን፣ ሆላንድ እና ሌሎችም ሀገራት መሪዎች የእንኳን ደስ ለዎት መልዕክታቸውን ለዶናልድ ትራምፕ ልከዋል፡፡
የዩክሬን እና ሩሲያን ጦርነት በተመረጡ በማግስቱ እንደሚስቆሙ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተናገሩት ዶናልድ ትራምፕ ከፕሬዝዳንት ዘለንስኪ እንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ደርሷቸዋል፡፡