ጌዲዮን ጥሞቲዮስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተለያዩ ተቋማት አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመዋል።

በዚህም መሰረት ጌዲዮን ጥሞቲዮስ (ዶ/ር) በቅርቡ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ተደርገው በተሾሙት ታዬ አጽቀስላሴ ምትክ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት በተጨማሪም ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የፍትህ  ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል።

ወ/ሮ ሃና አርዓያሥላሴ ፍትህ ሚኒስትር ተደርገው ከመሾማቸው በፊት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም ከዚያ በፊት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

እንዲሁም የመንግስት ኮሙንኬሽን ምክትል ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የቱርዝም ሚንስትር ተደርገው መሾማቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ በመሆን በማገልገል ላይ የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፤ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ተክተው የቱሪዝም ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት ላለፉት ዘጠኝ ወራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ የኢትዮጵያ አምስተኛው ፕሬዝዳንት ተደርገው መሾማቸው አይዘነጋም፡፡

ፕሬዝዳንት ታዬ ኢትዮጵያ ካሏት ነባር ዲፕሎማቶች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ አሜሪካ እና ሌሎች በርካታ ሀገራት በአምባሳደርነት ገለገሉ ሲሆን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር ሆነውም ሰርተዋል፡፡

ላለፉት ስድስት ዓመታት የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሶስት ሳምንት በፊት በX ወይም በቀድሞው ትዊተር ገጻቸው ላይ “ዝምታ ነው መልሴ” የሚል ጽሁፍ ማጋራታቸው ይታወሳል፡፡

የፕሬዝዳንቱ ንግግር በማህበራዊ ሚዲየዎች ላይ ዋነኛ መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ያለፈ ሲሆን ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ ከሀላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *