የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሀንስ አያሌው ከኃላፊነት ለቀቁ

የልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሀንስ አያሌው ስራቸውን የለቀቁት “በፈቃዳቸውና በግል ምክንያት” መሆኑን ተናግረዋል።

በተጠባባቂነት የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳን ጌታቸው ዋቄ ሀለፊነቱን እንደተረከቡ ተገልጿል።

ዮሀንስ አያሌው በስራ ዘመናቸው ባንኩ ከነበረበት ውስብስብ ችግርና ክስረት  ወደ ተሻለ አቋም እንዲመለስ ማስቻላቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች ይመስክሩላቸዋል።

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጠለቅ ያለ እውቀት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ዶክተር ዮሀንስ አያሌው ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክን በምክትል ገዥነት እና በዋና ኢኮኖሚስትነት አገልግለዋል።

በዚህም በገንዘብ ኢኮኖሚስትነታቸው ብዙዎች የሚያደንቋቸው ሲሆን ከአምስት አመት በፊት የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በቦርድ አባልነት አገልግለዋል፡፡

የቀድሞው የልማት ባንኩ ፕሬዝዳንት ሀይለኢየሱስ በቀለ ሲለቁ የተኩት ዮሃንስ የባንኩ ፕሬዝዳንት በመሆን ለአራት አመታት የባንኩን ፖሊሲ  መርተዋል ሲል ዋዜማ ሬዲዮ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ዶክተር ዮሀንስ በፕሬዝዳንትነት መምራት ከመጀመራቸው በፊት ባንኩ የገባበት ችግር ይዘጋ አይዘጋ የሚል ክርክር ላይ የደረሰ እንደነበረ ይነሳል።

ለዚህም ማሳያው የባንኩ ያልተመለሰ የብድር ምጣኔ ለልማት ባንኮች ከተቀመጠው የ15 በመቶ ገደብ አልፎ 57 በመቶ መድረሱ እና እጅግ በከፋ ችግር ውስጥ በመግባቱ ነበር።

በገንዘብ ሲታይም የባንኩ ያልተመለሰ ወይንም የተበላሸ የብድር ምጣኔ 27 ቢሊየን ብር ነበር።

ሆኖም አሁን በጤና ምክንያት እንደለቀቁ የተናገሩት ዶክተር ዮሀንስ በርካታ ያልተመለሰ ብድር ያለባቸውን ፋብሪካዎች አንድም ባንኩ ራሱ እንዲያስተዳድራቸው በማድረግ ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የካፒታል ችግር ያለባቸውን ባንኮች ተጨማሪ ብድር እንዲያገኙ አድርገው ከችግር እንዲወጡ ማድረጋቸው በስኬት ይነሳላቸዋል፡፡

እንዲሁም ለአንዳንድ ፋብሪካዎች ደግሞ አጣማሪ በማፈላለግ እንዲቋቋሙ አድርገው በርካታ ፋብሪካዎችን ወደ ብድር ከፋይነት እንዲመለሱ አድርገዋል።

በዚህም የባንኩ ያልለመለሰ የብድር ምጣኔ ከ57 በመቶ ወርዶ ፤ ከሚፈቀድለት 15 በመቶ ዝቅ ብሎ አሁን ላይ 6 በመቶ ከመድረሱ ባለፈ በየዓመቱ ትርፋማ እንዲሆን እንዳደረጉ ተገልጿል፡፡

አቶ ዮሀንስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተደርገው በተሸሙበት ወቅት የባንኩ የተጣራ ሀብት 3 ቢሊየን ብር የነበረ ሲሆን አሁን ላይ የተቋሙ የተጣራ ሃብት 40 ቢሊየን ብር ደርሷል፡፡

እንዲሁም አጠቃላይ የባንኩ ካፒታልም 182 ቢሊየን ብር መድረሱን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *