በአዲስ አበባ ያለው ከባድ አየር ንብረት የአውሮፕላን በረራዎችን አስተጓጎለ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ በተከሰተው ከፍተኛ ጭጋጋማ አየር ምንክንያት ወደ ሌላ አየር ማረፊያዎች እያዘዋወረ መሆኑን አስታወቀ

በአዲስ አበባ በተከሰተዉ ከፍተኛ ጭጋጋማ አየር አብዛኛው በረራዎች ቦሌ አዉሮፕላን ማረፊያ ሊያርፍ ባለመቻሉ ምክንያት ወደ ሌላ አየር ማረፊያዎች እንዲቀየሩ መደረጉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል ።

አየር መንገዱ እንደገለፀው ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ባለዉ ከፍተኛ ጭጋግ ( ጉም) ምክንያት የአየር ማረፊያዎችን ወደ ሌላ ቦታ እያዘዋወረ መሆኑን እና ይህም በሀገር ዉስጥ እና በአለም አቀፍ በረራዎች ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል ብሏል።

በተጓዦች ላይ ለደረሰዉ መጉላላት ይቅርታ የጠየቀው አየር መንገዱ በተጓዦች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ መጉላላቶችን ለመቀነስ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አውሮፕላን ጣቢያ ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን ከሁለት ሳምንት በፊት መግለጹ ይታወሳል።

በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው አዲሱ አውሮፕላን ጣቢያ በቢሾፍቱ ከተማ ልዩ ስሙ አቡሴራ በተባለው ስፍራ እንደሚገነባ ገልጿል።

ይህ አውሮፕላን ጣቢያ ወይም ኤርፖርት የሚገነባው በዓመት 25 ሚሊዮን መንገደኞችን ብቻ የማስተናገድ ያለው ቦሌ ዓከም አቀፍ ኤርፖርትን ለመተካት እንደሆነ የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

በቢሾፍቱ ልዩ ስሙ አቡ ሴራ በተባለው ስፍራ የሚገነባው ይህ ኤርፖርት ግንባታ ዲዛይን ዳር የተሰኘው ኩባንያ መመረጡንም አቶ መስፍን ገልጸዋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *