በኢትዮጵያ ማየት አቁመው ለነበሩ 217 ሰዎች የአይን ንቅለ ተከላ ተደረገላቸው

በኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት ለ217 ሰዎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተደርጎ የአይን ብርሃናቸው ተመለሰ

በኢትዮጰያ ባለፉት አስራ አንድ ወራት ለ217 ሰዎች የዓይን ብሌን ንቅለ ተከላ ህክምና በማድረግ የአይን ብርሃናቸው እንደተመለሰ የኢትዮጰያ ደም እና ህብረ- ህዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሀብታሙ ታዬ ተናግረዋል፡፡

የተለገሰው የአይን ብሌን ንቅለ ተከላውን ለሚያከናውኑት የተለያዩ የህክምና ተቋማት በመሰራጨት በአይን ብሌን ምክንያት ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎች ላይ ቅድመ ምርመራ በማድረግ  ልገሳው  እንደተከናወነ  ተገልጿል፡፡

በቀጣይ 445 የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸው ካለፈ በኋላ የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ ቢሆንም ከፈላጊዎች አንጻር በጣም ዝቅተኛ ነው ተብሏል።

ከሞት በኃላ ሰዎች የአይን ብሌናቸውን እንዲለግሱ በአዲስ አበባ ብቻ የማሰባሰብ ስራ የሚከናወን ሲሆን ፣በሀዋሳ፣ ጅማ ፣ ጎንደር እና መቀሌ በሚገኙ የህክምና ተቋማት ንቅለ ተከላው የሚከናወን ሲሆን በቀጣይ የአይን ብሌን ማሰባሰብ ስራው በክልሎች እንደሚደረግ አቶ ሀብታሙ ታዬ ተናግረዋል፡፡

የአይን ብሌን ከለጋሾቹ ላይ ከተነሳ በኃላ ለአስራ አራት ቀናት ማለትም ለሁለት ሳምንት ብቻ መቆየት እንደሚችል ተገልፆል፡፡

በ2006 የተደረገ ጥናት እንደሚያመላክተው እንደ ሀገር 300ሺ የሚሆኑ ሰዎች በአይን ብሌን ጠባሳ ብቻ የአይን ብርሃናቸውን ያጡ ሰዎች እንዳሉ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በኢትዮጵያ የአይን ህክምና ዋነኛ የህብረተሰብ ችግር ሲሆን በተለይም ትራኮማ በርካታ ዜጎች የአይን ብርሃናቸውን እንዲያጡ ከሚያደርጉ ዋነኛ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው፡፡

የአይን ህክምና ስፔሻሊስቶች እጥረት፣ ድህነት እና ስለ አይን ጤና አጠባበቅ ዝቅተኛ አመለካከት መኖር በኢትዮጵያ በአይን ጤና ችግር ምክንያት የማየት እድላቸውን እንዲያጡ አድርጓል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *