ራስ ገዞቹ ሶማሊላንድ እና ፑንትላንድ ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆሙ ተናገሩ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ከአራት ወራት በፊት በወደብ ጉዳይ በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።

ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት እንድትሆን ሶማሊላንድ ደግሞ የሀገርነት እውቅና እንድታገኝ የሚያደርግ በመሆኑ ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አድርጋ በምታያት ሶማሊያ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣንና እና ተቃውሞን አስከትሏል።

ከትናንት በስቲያም ሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደርን በ72 ሰዓት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቃ እንድትወጣ እና በሀርጌሳ እና ጋሮዌ ያሉ የኮንሱላ ጽህፈት ቤቶች እንዲዘጉ ሰራተኞቹም በሁለት ሳምንት ውስጥ ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ መወሰኗን አስታውቃለች፡፡

ራስ ገዟ ሶማላንድ እና ፑንት ላንድ የሶማሊያ መንግስት በሀርጌሳ እና ጋሮዌ የሚገኙ ቆንስላዎች እንዲዘጉ ያሳለፈውን ውሳኔ መቃወማቸው ተነግሯል።

ይህንን ተከትሎም ሶማሊያ የተለያዩ ዲፕሎማያዊ እርምጃዎችን ስትወስድ የቆየች ሲሆን፤ ባሳለፍነው ሀሙስም በኢትዮጵያ ላይ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ይፋ አድርጓል።

በዚህ መሰረትም በራስ ገዞቹ ሶማሊላንድ እና ፑንትላንድ ዋና ከተማ በሆኑት ሀርጌሳ እና ጋሮዌ ያሉ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች እንዲዘጉ ውሳኔ አሳልፋለች።

በተጨማሪም በሁለቱ ቆንስላዎች ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶችና ሰራተኞች በአንድ ሳምንት ውስጥ ሶማያ ለቀው እንዲወጡ ውሳኔ ማሳለፉም ይታወሳል።

እንዲሁም የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው  የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሃመድ ዋሬ ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ የ72 ሰዓት ግዜ መስጠቱም ይታወቃል።

በተጨማሪም ሶማሊያ በአዲስ አበባ የሚገኙትን አምባሳደሯን ለውይይት ወደ ሞቃዲሾ መጥራቷንም ሚኒስቴሩ አስታውቆ ነበር።

ይህንን ተከትሎም ራስ ገዟ ሶማሊላንድ እና ፑንት ላንድ የሶማሊያ መንግስት በሁለቱ ግዛቶች ያሉ ቆንስላዎች እዲዘጉ ያሳለፈውን ውሳኔ አውግዘዋል።

የሶማሊላንድ እና የፑንት ላንድ አስተዳደሮች የሶማሊያ መንግስት ቆንስላዎቹ እንዲዘጉ ያሳለፈውን ውሳኔ አንቀበልም ብለዋል።

የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምክትል ሚኒስትር ሮዳ ኤሊሴይድ ለሮይተርስ እንደተናገሩት “የሞቃዲሾ መንግስት የሚናገረው ምንም ይሁን ምን ቆንስላው ክፍት ሆኖ ይቆያል” ብለዋል።

የፑንትላንድ የማስታወቂያ ሚኒስትር መሀሙድ አይዲድ ድሪር ለአሜሪካ ድምፅ የሶማልኛ ቋንቋ አገልግሎት በሰጡት አስተያየት፤ “የሶማሊያ ውሳኔ አይሰራም” ብለዋል።

ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ እስካሁን ሶማሊያ ባሳለፈችው ጉዳይ እስካሁን አስተያየቷን ከመስጠት ተቆጥባለች፡፡

የፑንትላንድ ገንዘብ ሚኒስትር መሀመድ ፋራህ የተመራ ልዑክ ከሰሞኑ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከኢትዮጵያ ባለ ስልጣናት ጋር መክሮ ተመልሷል፡፡

ፑንትላንድ ከሰሞኑ ከሶማሊያ ፌደራል መንግስት ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን ያስታወቀች ሲሆን ይህን ባደረገች በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬት ጉብኝት አድርጋለች፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *