ኢትዮጵያ በግላስኮው የዓለም ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድርን በአምስተኛነት አጠናቀቀች

በስኮትላንድ ግላስጎ ሲካሄድ የቆየው የ2024 የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ፍጻሜውን አግኝቷል።

ከየካቲት 22 እስክ 24 2016 ዓ.ም ሲካሄድ በነበረው የ19ኛው የዓለም የቤት ዉስጥ ሻምፒዮና ከ130 በላይ ሀገራት  የተውጣጡ ከ650 በላይ አትሌቶቸ  መሳተፋቸው ተነግሯል።

ኢትዮጵያ በ800 ሜትር፣ በ1500 ሜትር እና በ3000 ሜትር  በሴትና በወንድ  በአጠቃላይ  በ8 ሴቶች እና በ5 ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች መሳተፏን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በሻምፒዮናው በሴቶች 800 ሜትር ፅጌ ዱጉማ እና በሴቶች 1500 ሜትር ፍሬወይኒ ሀይሉ የወርቅ፣ በሴቶች 3000 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ የብር እንዲሁም በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶች ሆነዋል።

በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ  ሁለት ወርቅ አንድ ነሀስ በአንድ ብር በአጠቃላይ በአራት ሜዳሊያዎች በማግኘት በሜዳልያ ሰንጠረዥ   ከአፍሪካ አንደኛ  ከአለም  አምስተኛ ደረጃን  በመያዝ ጨርሳለች ።

በሻምፒዮናው አሜሪካ 6 የወርቅ፣ 9 የብር እና 5 የነሃስ በድምሩ በ20 ሜዳያዎች በማግኘት ከዓለም አንደኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ቤሌጂየም በ3 የወርቅ እና አንድ የነሃስ በድምሩ በ4 ሜዳያዎች 2ኛ ደረጃን ስትይዝ፣ ኒውዚላንድ በ2 የወርቅ እና 2 የብር ሜዳሊያዎች 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች።

የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የዘንድሮው የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር በስኮትላንድ አዘጋጅነት የጠካሄደው የግላስኮው አትሌቲክስ ውድድር ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

በአትሌቲክስ ውድድሮች ላለፉት ዓመታት ስኬታማ የነበረችው ኬንያ በግላስኮው አትሌቲክስ ውድድር አንድ ነሀስ ሜዳሊያ ብቻ በማግኘት ከዓለም 27ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

አፍሪካ በዘንድሮው የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር አነስተኛ ሜዳሊያዎችን ያስመዘገበች ሲሆን ኢትዮጵያ እና ቡርኪናፋሶ ብቻ የወርቅ ሜዳሊያ የስመዘገቡ ሲሆን ኬንያ፣ እና አልጀሪያ አንድ የብር እና ነሀስ ሜዳሊያዎችን ያገኙ ሀገራት ናቸው፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *