ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጸጥታ እና ዲፕሎማሲ ተቋማት ላይ የአመራር ሹም ሽር አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አዳዲስ ሹመቶችን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው አጸድቀዋል፡፡

በዚህም መሰረት የብሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆኑ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቀድሞ አምባሳደር የነበሩት ታዬ አጽቀስላሴ ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነዋል፡፡

እንዲሁም ዶክተር መቅደስ ዳባ ደግሞ ከጤና ሚኒስትርነት ሀላፊነታቸው የመልቀቂያ ደብዳቤ ላሰገቡት ዶክተር ሊያ ታደሰ ምትክ ሆነው ተሾመዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የደህንነት አማካሪ የነበሩት ሬድዋን ሁሴን ደግሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይረክተር ተሹመዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሆነው ከመስራታቸው በፊት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኢታ፣በኤርትራ እና አየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡

ትዕግስት ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይረክተር ሆነው እንደተሸሙም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ዛሬ በይፋ መንግስታዊ ስልጣናቸውን ያስረከቡት አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ላለፉት 11 ዓመታት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ከሶስት ዓመት በፊት ደግሞ አቶ ደጉ አንዳርጋቸውን ተክተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሀላፊነትን ይዘው ቆይተዋል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን ለረጅም ዓመታት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ከሶስት ዓመት በፊት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በመተካት ነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታ ደርበው የያዙት።

በቀድሞው ኢህአዴግ እና በአሁኑ ብልጽግና ፓርቲው ውስጥ ቁልፍ ሥልጣንን ይዘው የቆዩት አቶ ደመቀ ፤ በብልፅግና ፓርቲ ካሉት ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች መካከል አንዱ ነበሩ።

አቶ ደመቀ ከሀላፊነት የተነሱት ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ብልጽግና ፓርቲ ነባር አመራሮችን በአዲስ አመራሮች ለመተካት ባለው እቅድ መሰረት እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናግረዋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *