ኢትዮጵያ ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራን ከሁለት ዓመት በኋላ እንደምታካሂድ ገለጸች

በኢትዮጵያ የህዝብ እና ቤት ቆጠራ ከተደረገ 17 ዓመት የሆነው ሲሆን የሕዝብ ቁጥሯን በየዓመቱ 10 በመቶ እየጨመረች እየቆጠረች ትገኛለች፡፡

የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የጦርነት እና ጸጥታ ችግሮች የሕዝብ ቆጠራውን ለማካሄድ እንቅፋት ሆኖ የቆየ ሲሆን በየጊዜው የፕሮግራም ማራዘም ስታደርግም ነበር፡፡

ከሶት ዓመት በፊት ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ ለማድረግ አራት ቢሊዮን ዶላር በጀት ተመድቦ የባለሙያ እና ቁሳቁስ ዝግጅት የተጀመረ ቢሆንም በሀገሪቱ ባጋጠመ ጦርነት ምክንያት ሳይካሄድ ቆይቷል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ 4ኛዉ የህዝብ እና ቤት ቆጠራን እስከ 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ለማከናወን ማቀዱን አስታውቋል።

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ይህንን ያስታወቀው ለሶስት ዓመታት በፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ስታትስክስ አገልግሎት የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።

በኢትዮጵያ የህዝብና ቤት ቆጠራ በየአስር አመቱ የሚከናወን ቢሆንም ለመጨረሻ ጊዜ የተቆጠረው በ1999 ዓ.ም ነው።

4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ በ2009 ዓ.ም መከናወን የነበረበት ቢሆንም በሀገሪቱ በነበሩ የፀጥታ ችግሮች በኃላም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በአለማቀፍ መስፈርት የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እንዳልነበር ተገልጿል።

ይህንን ተከትሎ ከ2016 ዓ.ም እስከ 2018 በሚተገበር የኢትዮጵያ ስታስቲካል ልማት ፕሮግራም የህዝብና ቤት ቆጠራ በፕሮግራሙ ተካቷል ተብሏል፡፡

ይህዝብ ቆጠራዉን ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የሚጠይቅ በመሆኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸውና እስከ 2018 ዓ/ም ባለው ጊዜ ለማድረግ መታቀዱ ተጠቁሟል።

እንደ ተባበሩት መንግስታት ስነ ህዝብ ፖሊሲ ከሆነ በኢትዮጵያ የሕዝብ ብዛት 129 ሚሊዮን 719 ሺህ 719 ሲሆን ዓመታዊ የውልደት መጠኑም 2 ነጥብ 5 በመቶ ነው፡፡

የአፍሪካ ቁጥር አንድ የሕዝብ ብዛት ያላት ሀገር ናይጀሪያ ስትሆን ጠቅላላ ይህዝብ ብዛቷም 229 ሚሊዮን 152 ሺህ ደርሷል ተብሏል፡፡

ሶስተኛዋ የአፍሪካ ባለግዙፍ የህዝብ ብዛት ያላት ሀገር ግብጽ ስትሆን 114 ሚሊዮን ህዝብ አላት፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *