ዳሸን ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎችን ሸለመ

ዳሸን ባንክ ባዘጋጀው ሁለተኛው ዙር የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ተሳትፈው ያሸነፉ ተወዳዳሪዎችን ሸልሟል፡፡

ባንኩ ለውድድሩ አሸናፊዎች ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጌያለሁ ያለ ሲሆን ለአሸናፊዎች ከግማሽ ሚሊዮን ብር እስከ100 ሺህ ብር ሸልሟል።

በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ባንኩ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከነደፋቸው ትልልቅ መርሃ ግብሮች አንዱ ይህ የስራ ፈጠራ ውድድር መሆኑን ጠቁመው በመርሃ ግብሩ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ስድስት ሺህ  ተወዳዳሪዎችን ማሳተፍና ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል፡፡

አቶ አስፋው ለውድድሩ አሸናፊዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ያሉ ሲሆን ባንኩ ለወደፊት አብሯቸው እንደሚሰራና ድጋፍ እንደሚያደርግላቸውም ቃል ገብተዋል፡፡

ለመጨረሻው ዙር የደረሱ ተወዳዳሪዎች እያንዳንዳቸው የተለያየ መጠን ያለው ሽልማት ያገኙ ሲሆን አንደኛ ለወጣ አሸናፊ 500 ሺህ ብር ሁለተኛ ለወጣው ደግሞ 400 ሺህ ብር ሶስተኛ ለወጣው 300 ሺህ ብር እንዲሁም አራተኛው እና አምስተኛ ለወጡት ደግሞ ለወጡ 200 ሺህ እና 150 ሺህ ብር ተሸልመዋል።

እንዲሁም ከስድስተኛ እስከ 10ኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 100 ሺህ ብር መሸለሙን አስታውቋል።

ባንኩ በአጠቃላይ ለስራ ፈጣሪ ተወዳዳሪ አሸናፊዎች ብር ከ2 ሚሊዮን በላይ ብር ወጭ እንዳደረገ ገልጿል።

በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለውድድሩ ተሳትፎ ጥሪ መደረጉን ተከትሎ ከ6000 በላይ ተወዳዳሪዎች በባንኩ ቅርንጫፎችና ዋናው መስሪያ ቤት የውድድር ንድፈ ሃሳባቸውን አቅርበው ተወዳድረዋል።

ከውድድሩ በፊት በስድስት ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ሃዋሳ፣ ባህር ዳር እና ደሴ ከተሞች ስልጠና እንዲሰጥ መደረጉን ባንኩ አስታውቋል፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *