በስፔኗ ቫሌንሲያ የተካሄደው የማራቶን ውድድር በኢትዮጵያዊያን የበላይነት ተጠናቀቀ፡፡
ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ የሚነግሱባት የስፔኗ ቫሌንሲያ ዛሬም ኢትዮጵያዊያን ተመሳሳይ ድሎችን አግኝተውባታል፡፡
በዚው ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በአንደኝነት አጠናቀዋል፡፡
በሴቶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን ከአንደኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በበላይነት ሲያሸንፉ አትሌት ውርቅነሸ ደገፈ፣ አልማዝ አያና እና ህይወት ገብረኪዳን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ጠናቀዋል፡፡
በዚህ የወንዶች የማራቶን ውድድር ላይ አትሌት ሲሳይ ለማ አንደኛ፣ ኬንያዊው አትሌት አሌክሳንደር ሙቲሶ ሁለተኛ እንዲሁም ዳዊት ወልዴ እና ቀነኒሳ በቀለ ሶተኛ እና አራተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡
አትሌት ሲሳይ ለማ ርቀቱን 2:01:48 በሆነ ሰአት ማጠናቀቅ የቻለ ሲሆን የቦታውን ክብረወሰን ማሻሻል ሲችል ተጠብቆ የነበረው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡
በሀገር አቋራጭ፣ አምስት ሺህ እና 10 ሺህ ውድድሮች ላይ ለዠዓመታት ስኬታማ የነበረው የ41 አመቱ ስኬታማው ቀነኒሳ ውድድሩን ለመጨረስ 2:04:19 የሆነ ሰአት ሲፈጅበት የአለም አንጋፋዎችን የማራቶን ክብረወሰን አሻሽሏል።
አትሌት ቀነኒሳ በአምስት እና አስር ሺህ ውድድሮች ላይ ለዓመታት ሳይረታ የቆየ ውጤታማ አትሌት ሆኖ ቆይቷል።
በሁለቱም ርቀቶች የዓለም ሪከርዶችን ለ16 ዓመታት ይዞ የቆየው አትሌት ቀነኒሳ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ፊቱን ወደ ማራቶን ውድድር አዙሯል።
የማራቶን ውድድርን ከሁለት ሰዓት በታች ይገባል ተብሎ ከሚጠበቁት የዓለም ማራቶን ሯጮች መካከል ዋነኛው ነውም ተብሏል።
አትሌት ቀነኒሳ በዓለም የሀገር አቋራጭ ውድድሮች የምንጊዜውም ስኬታማ አትሌት ሲሆን 11 ጊዜ የሀገር አቋራጭ ውድድሮችን በአንደኝነት አጠናቋል።
በጀርመን አዘጋጅነት በ2009 በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር በአምስት ሺህ እና 10 ሺህ ውድድሮችን በአንደኝነት ማጠናቀቅም ችሏል።
በ2014 በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ያስመዘገበው ውጤት ስድስተኛው የምንግዜውም ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል።
ከሁለት ዓመት በኋላም በ2019 በርሊን ማራቶንን በ2:01:41 ሰዓት በአንደኝነት ያጠናቀቀ ሲሆን ከቀናት በኋላ በቫሌንሲያ በሚካሄደው የማራቶን ውድድር ላይ ለውጤት ይጠበቃል።