03
Dec
በስፔኗ ቫሌንሲያ የተካሄደው የማራቶን ውድድር በኢትዮጵያዊያን የበላይነት ተጠናቀቀ፡፡ ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ የሚነግሱባት የስፔኗ ቫሌንሲያ ዛሬም ኢትዮጵያዊያን ተመሳሳይ ድሎችን አግኝተውባታል፡፡ በዚው ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በአንደኝነት አጠናቀዋል፡፡ በሴቶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን ከአንደኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በበላይነት ሲያሸንፉ አትሌት ውርቅነሸ ደገፈ፣ አልማዝ አያና እና ህይወት ገብረኪዳን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ጠናቀዋል፡፡ በዚህ የወንዶች የማራቶን ውድድር ላይ አትሌት ሲሳይ ለማ አንደኛ፣ ኬንያዊው አትሌት አሌክሳንደር ሙቲሶ ሁለተኛ እንዲሁም ዳዊት ወልዴ እና ቀነኒሳ በቀለ ሶተኛ እና አራተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡ አትሌት ሲሳይ ለማ ርቀቱን 2:01:48 በሆነ ሰአት ማጠናቀቅ የቻለ ሲሆን የቦታውን ክብረወሰን ማሻሻል ሲችል ተጠብቆ የነበረው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ አራተኛ ሆኖ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡…