ስድስት ዩንቨርሲቲዎች የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ ተገለጸ

ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎችን እንደሚመድብ ገልጿል፡፡

ይሁንና ስድስት የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች የሬሚዲያል ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ አስታውቋል፡፡

የሬሚዲያል ተማሪዎችን ከማይቀበሉ ዩንቨርሲቲዎች መካከልም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ አርሲ ዩኒቨርሲቲ እና ኮተቤ የትምህርት ዪኒቨርሲቲዎች ናቸው፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር እነዚህ ዩንቨርሲቲዎች ለምን የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎችን እንደማይቀበሉ ምክንያታቸውን አልጠቀሰም፡፡

በ2015 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ 845 ሺሕ 099 ተማሪዎች ውስጥ፤ 817 ሺሕ 838 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በታች የሆነ ውጤት ማምጣታቸው ይታወሳል፡፡

የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ከአጠቃላይ 845 ሺሕ 099 ተፈታኞች ውስጥ 27 ሺሕ 267 ተማሪዎች ወይንም (ሦስት ነጥብ ኹለት በመቶ ብቻ) 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት አምጥተዋል።

በተፈጥሮ ሳይንስ ከተፈተኑ 356 ሺሕ 878 ተማሪዎች ውስጥ 19 ሺሕ 017 ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ሲመጡ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከተፈተኑ 488 ሺሕ 221 ተማሪዎች ውስጥ 7 ሺሕ 250 ተማሪዎች ብቻ 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት እምጥተዋል።

በአጠቃላይ ከማኅበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ ከ500 በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች 10 ብቻ ሲሆኑ፤ ከተፈጥሮ ሳይንስ ደግሞ 263 ተማሪዎች 600 እና ከዛ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል ተብሏል።

በተጨማሪም በማታ ከተፈተኑ 16 ሺሕ 541 ተማሪዎች ውስጥ ያለፉት 12 ተማሪዎች ብቻ ሲሆኑ በግል የተፈተኑ 169 ሺሕ 502 ተማሪዎች ውስጥ ያለፉ 498 ተማሪዎች ብቻ ናቸው፡፡

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *