ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ የፋው ምርት የሆኑ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ አቀረበ

የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ ገበያዎች በማምጣት የሚታወቀው ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ አሁን ደግሞ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ማስመጣቱን ገልጿል።

ኩባንያው የቻይናው ፋው ሰራሽ የሆኑ የተለያዩ መጠን የመጫን አቅም ያላቸው አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከባድ እቃዎችን ሙጫን እሚችሉ የጭነት ተሽከርካሪዎችን አስመጥቷል።

ፈርስት አውቶሞቲቭ ዎርክስ ወይም ፋው በመባል የሚታወቀው የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ ዋና መቀመጫውን ቻይና በማድረግ ከፈረንጆቹ 1950ዎቹ ጀምሮ በማምረት ላይ ይገኛል።

ድርጅቱ በ2021 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎችን ለዓለም በመሸጥ ቀዳሚ የዓለማችን ኩባንያ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ የቻይና ኩባንያ ከኢትዮጵያው ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ጋር አብሮ መስራቱን የገለጸ ሲሆን እስከ 20 ቶን እቃ የመጫን አቅም ያላቸው ተሽኩርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረቡን አስታውቋል።

ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች መሸጫ እድሳት በአዲስ አበባ መክፈቱን የገለጸ ሲሆን በቅርቡም በሐዋሳ ተጨማሪ ሱቆችን እከፍታለሁ ብሏል።

ለኢትዮጵያ ገበያ የቀረቡት እነዚህ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ቆጣቢ እና ቀልጣፋ እንደሆኑም ተገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *