በኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ስራዎችን የሰሩ ሰዎች ተሸለሙ

በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በርካታ የበጎ አድራጎት ስራ የሰሩ ሰዎችን ማመስገን እና ለስራቸው እውቅና መስጠት አላማው ያደረገ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

ማስተር አብነት ፣ ወንድም ካሊድ ፣ሚኪያስ ለገሰ እና ዘካሪያስ ኪሮስ በኢትዮጵያ ዘር፣ ቀለም እና ሀይማኖት ሳይገድባቸው የተቸገሩ ወገኖችን ለዓመታት እየረዱ መሆናቸው በመድረኩ ላይ ተጠቅሷል።

ግለሰቦቹ ለሰሩት በጎ ስራ በሽማግሌዎች ምርቃት ታጅበው የምስጋና እና የእውቅና መርሀግብር ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ ስቴይ ኢዚ ሆቴል በተካሄደው በዚህ ፕሮግራም ላይ የመንግስት አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል።

ምስጋና እና እውቅና ከተሰጣቸው ሰዎች መካከልም በአዲስ አበባ በበጎ ስራቸው  የተቸገሩ ሰዎች እንዲረዱ እና ህክምና  እንዲያገኙ በማድረግ የሚታወቁት ሚኪያስ ለገሰ ( የሰሊሆም የአዕምሮ መርጃ ማዕከል) መስራች ፣ ማስተር አብነት ከበደ ፣ ወንድም ካሊድ ፣ዘካሪያስ  ኪሮስ ( የእማማ ዝናሽ ወዳጅ)   ዋነኞቹ ናቸው።

የምስጋና እና እውቅና ፕሮግራሙ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከኤሴቅ ዲኮር እና የኤቨንት ኦርጋናይዘር ጋር በመተባበር “የህይወት ልምዴን ለአዲሱ ትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ ተካሂዷል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *