ኢትዮጵያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የጣለችውን ገደብ አነሳች

በኢትዮጽያ ለወራት ያህል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ ተነስቷል።

በኢትዮጵያ ከየካቲት ወር መጀመሪያ አንስቶ በኢንተርኔት አገልግሎቶች ማለትም በፌስቡክ፣ ሜሴንጀር፣ ቴሌግራም እና ቲክቶክ ላይ ገደብ መጣሉ ይታወሳል።

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት ገደብ መጣሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ በርካታ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች መንግሥት ገደቡን እንዲያነሳ ሲጠየቅ ቆይቷል።

በኢንተርኔት እገዳው ምክንያትም ኢትዮጵያ 7 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ ማጣቷን የመብቶችና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል ገልጿል፡፡

“ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶችን ተከትሎ፤ ከ2008 ወዲህ የበይነመረብ ግንኙነትን ማቋረጥ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣ ችግር ነው” ያለው ማዕከሉ፤ የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጡ የዴሞክራሲና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት ጸር መሆኑን አመላክቷል፡፡

መንግሥት ዋና ዋና የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች በኢትዮጵያ እንዳይጎበኙ እገዳ መጣሉ ሕጋዊ መሰረት የሌለው ነው ሲልም ገልጿል፡፡

የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጥ ትኩረት ሊያገኝ ባለመቻሉም የሰብዓዊ መብቶች እሴቶችን እንዲሁም በሕገ መንግሥቱ የተጠበቁ የሰብዓዊ መብቶችንና ነፃነቶችን እየገፈፈ ነውም ተብላል።

በዚህም በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ በተጣለው ገደብ ከ140 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር በላይ የኢኮኖሚ እንዲሁም፤ 27 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር የውጭ ቀጥታ የምርት ገበያ ኪሳራ ማድረሱን እና 2 ሺሕ 372 ሰዎች ሥራ እጥ እንዲሆኑ ማድረጉንም ማዕከሉ በሪፖርቱ አስታውቋል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *